የመኪና አስገራሚ እውነታዎች እና በኢትዮጵያ የመጀመርያው መኪና
የመኪና አስገራሚ እውነታዎች እና በኢትዮጵያ የመጀመርያው መኪና

የመኪና አስገራሚ እውነታዎች እና በኢትዮጵያ የመጀመርያው መኪና

December 16, 2024
0 Comments

የመኪና አስገራሚ እውነታዎች

•የዓለማችን የመጀመሪያዋ መኪና የተሰራችው እ.ኤ.አ በ1885 ካርል ቤንዝ በተባለ ሰው ሲሆን የመኪናዋ ከፍተኛ ፍጥነት በሰዓት 16 ኪ.ሜ ነበር።

•በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የነበሩ መኪናዎች 40 በመቶ በእንፋሎት፣ 38 በመቶ በኤሌትሪክ እንዲሁም 22 በመቶ በጋዝ ግብዐት የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ነበሩ።

•መኪና ውስጥ ሬዲዮ መግጠም የተጀመረው በ1920ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ሲሆን በወቅቱ ቴክኖሎጂው ‘የአሽከርካሪዎችን ትኩረት በመስረቅ ለአደጋ ያጋልጣል’ በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር።

•የዓለማችን የመጀመሪያው የመኪና ውድድር የተካሄደው እ.ኤ.አ በ1895 ነበር። በወቅቱ የመኪናዎች ከፍተኛው ፍጥነት 24 ኪ.ሜ በሰዓት ነበር።

•የመኪና ቀበቶ (ሲት ቤልት) ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው እ.ኤ.አ በ1959 ነው። ሲት ቤልት በየ6 ደቂቃው ልዩነት አንድን ሰው ከሞት እንደሚታደግ ጥናቶች ያመለክታሉ።

•ኤር ባግ (የመኪና የአየር ከረጢት) ለመጀመሪያ ጊዜ መኪናዎች ላይ የተገጠመው እ.ኤ.አ በ1974 ነው።

•ዓለም ላይ ከ1.4 ቢሊዮን በላይ መኪናዎች የሚገኙ ሲሆን ይህ ቁጥር አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ መኪናዎችን ብቻ የሚወክል ነው።

•በዓለማችን በየቀኑ ከ150 ሺህ በላይ መኪናዎች ይመረታሉ።

•አንድ መኪና በአማካኝ 30 ሺህ የሚደርሱ ክፍሎች ያሉት ሲሆን 80 በመቶ የሚሆነው የመኪና ክፍል ደግሞ በጥገና መልሶ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል ነው።

•የዓለማችን ግዙፉ የመኪና አምራች ኩባንያ ቶዪታ ነው ሲሆን በዓመት ከ10 ሚሊዮን መኪና በላይ ያመርታል።

•በዓለማችን አብዛኞቹ የቅንጦት መኪና አምራች ኩባንያዎች የቮልስ ዋገን ንብረቶች ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ ቤንትሊ፣ ቡጋቲ፣ ላምቦርጊኒ፣ አውዲ፣ ዱካቲ እና ፖርሽ ይጠቀሳሉ።

•95 በመቶ የመኪኖች የአገልግሎት ዘመን የሚያልፈው በቆሙበት አልያም ሳይነዱ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

•በዓለማችን በየአመቱ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በመኪና አደጋ ሲሞቱ፣ 50 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡

መኪና ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የገባው በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት በ1900 ዓ.ም ነው፡፡ እንግሊዝ ሰራሿን ይህቺን መኪና ለመጀመሪያ ጊዜ ያሽከረከሩትም ንጉሱ እንደነበሩ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡

የመጀመሪያዋ መኪና ወደ አዲስ አበባ የገባችው (የደረሰችው) ከዛሬ 117 ዓመታት በፊት ታኅሣስ 20 ቀን 1900 ዓ.ም ነበር፡፡

ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ኢትዮጵያን ለማዘመን በነበራቸው ፍላጎት መኪና ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ያላቸውን ጉጉት የሰማው እንግሊዛዊ ቤንትሌይ፣ ዌልስ ከተባለ ጓደኛው ጋር በመሆን የታርጋ ቁጥሯ ‹‹D3130››የሆነች አውቶሞቢል ይዘው መኪናዋን በመርከብ ጭነው በባህር ላይ ጉዞጀመሩ፡፡

ጅቡቲን አልፈው ድሬዳዋ ደረሱ፡፡ ደማቅ አቀባበልም ተደረገላቸው፡፡ ከዚያምበሐረር የሚገኙ መሳፍንትና መኳንንት መኪናዋን ማየት ስለፈለጉ መኪናዋን ይዘው ወደ ሐረር ሄዱ፡፡ በዚያ አካባቢም ጥቂት ሰንብተው ወደ አዲስ አበባ ጉዞ

ጀመሩ፡፡

ታኅሣሥ 20 ቀን 1900 ዓ.ም አዲስ አበባ ሲደርሱ 2000 ባለፈረሰኛ ሰራዊት

የክብር አቀባበል አደረገላቸው፤ መድፍ ተተኮሰ፡፡ እንግሊዛውያኑ የመኪናዋ

አሽከርካሪዎችም የመኪናዋን ጥሩምባ እየነፉ አቀባበሉን አደመቁት፤ ፈረሶቹ ግን

እየደነበሩ አስቸገሩ፡፡

ታኅሣሥ 21 ቀን 1900 ዓ.ም እንግዶቹ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ገብተው ግብዣ

ተደረገላቸው፡፡ በማግሥቱ ታኅሣሥ 22 ቀን 1900 ዓ.ም ከረፋዱ አምስት ሰዓት

ሲሆን ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ መኪናዋን አዯት፡፡

•ኢትዮጵያ ውስጥ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ መኪናዎች መኖራቸው ይገመታል፡፡

Add a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Categories

Recent Posts

About us

John Hendricks
Blog Editor
We went down the lane, by the body of the man in black, sodden now from the overnight hail, and broke into the woods..
Copyright © 2024. All rights reserved.